ታሪክ፣ ኪነ-ጥበብ፣ ባህልና እሴት ከውበት ጋር የተዳመሩባት ጊዶሌ ከተማ ቀጣይ የተስፋና የብልጽግና ቀጠና ናት፤ በከተማችን ማልማትና ማደግ ለምትፈልጉ የጋርዱላ ተራራ አናቶች ለሎጅ ፍጹም ማራኪና ውብ ናቸው፡፡ የታላቁ ስምጥ ሸለቆ አካል የሆነውና ማራኪው የጫሞ ሐይቅን በርቀት እየተመለከቱ በነፋሻ አየር የሚደመሙበት የጊዶሌ ተራራማ ስፍራዎች ነፍስን የሚያድስ ልዩ ጣዕም አላቸው፡፡ በሆቴል፣ በነዳጅ ማደያ፣ በሱፐርማርኬት፣ በትምህርት፣ በጤና፣ በፋብሪካና እንዲሁም በተለያዩ መስኮች መዋዕለ-ንዋያችሁን ለማፍሰስ ለተዘጋጃችሁ አልሚ ባለሀብቶችና ኢንቬስተሮች ከተማዋ ከ184 ሄክታር መሬት በላይ ዝግጁ አድርጋለች፡፡ ኑ-እደጉ፤ አብረንም እንደግ እንላለን፡፡

ለበለጠ መረጃ፡ Mayor Office – Gidole Town

  • 251930546607
  • 251916881505
  • 251467740605

www.gidoletown.gov.et

gidolemayor@gmail.com

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *